ክቡር አምባሳደር ዶ/ር ሙክታር ከድር KUSALA GREEN BIODIVERSITY ORGANIZATION የተባለው ድርጅት መስራች፣ የዳይሬክተሮች ቦርድ አመራር አባል እና Climate Change Specialist የሆኑት Mrs. Sentle Tabane በአገራችን ወቅታዊ ጉዳዮች፣በአገራችን የቱሪስት መስህብ ቦታዎች ፖቴንሽያልና አጠባበቅ፣በአየር ንብረት ለውጥና በአፍሪካዊ የጋራ ጉዳዮቻችን ላይ በጣም ጠቃሚ የሚባል ውይይት አካሂደዋል፡፡
 
ክቡር አምባሳደር በዚሁ ወቅት የአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ በዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡በህወሃት የተፈጠረው ጦርነት እንዳይጀመር አገራችን ያለፈችባቸውን በትዕግስት የተሞሉ ጊዜያት፣ተገደን የገባንበት ጦርነት እንደሆነና አሁን ጦርነቱ ቆሞ በአፍሪካ ህብረት ጥላ ሰር የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ አደራዳሪነት ጉዳዩ እልባት ሊያገኝ በሂደት ላይ መሆኑን፣ በዚሁም መሰረት በኢትዮጵያ በኩል በክቡር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የሚመራ 7 አባላት ያሉት የሰላም ተደራዳሪ ኮሚቴ ተደራጅቶ እየሰራ እንደሆነ፣ኢትዮጵያ ጦርነት የማትፈልግና ሁሌም ለሰላም ቁርጠኝነት እንዳላት አስረድተዋል፡፡እውነታው ይህ ቢሆንም በተሳሳተ ትርክት ላይ በመመስረት ታዋቂ ነን የሚሉ ሚዲያዎች አንዳንድ ምዕራባውያን አገሮችን እያሳሳቱት መሆኑን በማስረዳት ስለኢትዮጵያ በተገቢው ሁኔታ ትክክለኛውን መረጃ ሰጥተዋል፡፡
 
ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ዝቅተኛ አሉታዊ አስተዋጽዖ ያላት ሆና ሳለ በከፍተኛ ደረጃ ተጎጅ መሆኗን፣በዚህም ምክንያት ድርቅ እና የተለያዩ ጉዳቶች ሰለባ እንደሆነች፣ይህንኑ ታሳቢ በማድርግ አገራችን Green Development Strategy አውጥታ እየተገበረች እንደሆነ፤ኢትዮጵያ በአፍሪካ ፈጣን እድገት ከሚያስመዘግቡ ጥቂት አገራት አንዷ መሆኗን፣ የእድገቱን ቀጣይነት ለማረጋገጥ፣የግብርና መር ኢንደስተሪያላይዜሽን ጉዟችን ለማቀላጠፍ የኃይል አቅርቦት ማሳደግ ቁልፍ ተፈላጊነት ያለው ጉዳይ እንደሆነ፣ አገራችን ከፍተኛ የሆነ የታዳሽ ኃይል ፖቴንሽያል ያላት አገር እንደመሆኗ መጠን ይህንኑ የውሃ፣የንፋስና የጅኦ ተርማል ዕምቅ አቅም በመጠቀም ሃይል የማመንጨት ስራ እየሰራች መሆኑን፣በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ መሪነት ኢትዮጵያን አረንጓዴ የማልበስ/GREEN LEGACY/ መርሃ-ግብር ተነድፎ ባለፉት 3 ዓመታት 20 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን በተሳተፉበት ከ18 ቢሊዮን በላይ ዛፎች የተተከሉ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ ችግሩ የጋራ እንደመሆኑ መጠን መፍትሔውም የጋራ ነው በሚል አስተሳሰብ በመመራት ይህንኑ አረንጓዴ የማልበስ መልካም ተግባር በጎረቤት አገሮች በደቡብ ሱዳን፣በሶማሊያና በጅቡቲ የኢትዮጵያን ልምድ ለማስፋፋት የምስራቅ አፍሪካን የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳት የመታደግ የተቀናጁ ጥረቶች እየተካሄዱ ናቸው፡፡
 
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ/ GERD/ የታዳሽ ኃይል ማመንጫ ከሆኑት አንዱ ፕሮጄክት መሆኑን፣ፕሮጄክቱ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያውያን ባለቤትነትና ፋይናንስ እየተካሄደ መሆኑን፣ኢትዮጵያ የውሃው 86 በመቶ አመንጭ እንደሆነች፣ፕሮጄክቱን የምትገነባው ከህዝቧ ከ70 በመቶ በላይ ያለመብራት የሚኖረውን ህዝቧን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ለማድረግና በድህነት ውስጥ የሚገኘውን 60 በመቶ ህዝቧን ከድህነት ለማላቀቅ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ግብጽና ሱዳን የግድቡን ጉዳይ ወደ ተባበሩት መንግስታት መድረኮች ለመወሰድ ተደጋጋሚ ጥረት ኢትዮጵያ በጽኑ በምታምንበት ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ መርህ በመመራት ድርድሩ በአህጉራዊ ድርጅታችን የአፍሪካ ህብረት ማዕቀፍ ስር

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram