በደቡባዊ አፍሪካ የፐብሊክና ዲጅታል ዲፕሎማሲ ግብረ ኃይል በወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ የመረጃ ልውውጥ በማድረግ፣የቀጣይ ሥራዎችን ዕቅድ በማጽደቅ ያለፉትን ቀናት አፈጻጸም ገመገመ፡፡ክቡር አምባሳደር ዶ/ር ሙክታር ከድር የአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ በዝርዝር ያብራሩ ሲሆን መንግስት የሀገሩን ሉዓላዊነት፣የህዝቡን ሠላም እና የግዛት አንድነት ለማስከበር እያደረገ ያለው የመከላከል እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠሉን በማውሳት መንግስት አሁንም ለሰላም የዘረጋቸው እጆቹ እንዳልታጠፉ ገልጸዋል፡፡
 
በፐብሊክና ዲጅታል ዲፕሎማሲ የንቅናቄ ስራው በቅርቡ ከተጀመረ ወዲህ ኢትየጵያዊያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ለአገራዊ ጥሪ በአገራዊ ወኔና በአንድነት መንፈስ ያከናወኗቸው መልካም ጥረቶች ተጠናከረው እንዲቀጥሉ አምባሳደሩ ጥሪ አቅርበዋል።
 
ወቅታዊ አገራዊ ሁኔታን አስመልክቶ በፐብሊክ እና ዲጂታል ዲፕሎማሲ፣ በሀብት አሰባሰብ እና ሀገርን ከጥፋት ኃይሎች ለመታደግ ለሚፋለመው ጥምር ኃይል ተገንና ደጀን በመሆን ለመንቀሳቀስ በተዘጋጀው ማስፈጸሚያ ዕቅድ መሠረት በንቃት ለመሳተፍ ዝግጁ መሆናቸውን ተሳታፊዎቹ አረጋግጠዋል።
 
አገራችን የገጠማትን ፈተናዎች ለመሻገር በሚደረገው እልህ አስጨራሽ ተጋድሎ ሙሉ ተሳትፎ የማድረግ የዜግነት ግዴታ አለብን ያሉት ኢትዮጵያዊያኑ ወቅታዊ መረጃዎችን የሚያገኙበት ሁኔታ እና ከኢትዮጵያ ውጭ በተወለዱ ሁለተኛ ትውልድ ላይ ትኩረት ተደርጎ እንዲሠራም አሳስበዋል።
 
በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ለፍቶ አዳሪ ስለሆነና በማህበራዊ ሚዲያ ብቻ ስለማናገኘው በዲጅታል ዲፕሎማሲ የሚሰራው ስራ እንደተጠበቀ ሆኖ በአካል ተንቀሳቅሶ በፊት ለፊት መድረኮች በስፋት ሞቢላይዝ ማድረግ እንደሚገባል ተሳታፊዎቹ አስገዝበዋል።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram