“በሀገር ሉዓላዊነትና በህዝባችን ሰላም ላይ የተቃጣውን ጥቃት ለመቀልበስ የሚጠበቅብንን ሁሉ ድጋፍና ርብብር እናደርጋለን”
በፒተርማርዝበርግ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ!!
 
(ነሐሴ 28 ቀን 2014) አምባሳደር ዶ/ር ሙክታር ከድር፣ በደቡብ አፍሪካ የኢፌዲሪ ልዩ መልእክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር፣ በደቡብ አፍሪካ፣ ካዋዙሉናታል ፕሮቪንስ፣ ፒተርማርዝበርግ ከተማና በአካባቢው ከሚኖሩ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ጋር በአገራዊ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ መክረዋል፡፡
በመድረኩ ክቡር አምባሳደሩ የአሸባሪው ሕወሐት ቡድን ከለውጡ ማግስት አንስቶ የአገር ሉዓላዊነትን፣ የህዝቡን ሠላምን እና የግዛት አንድነትን አደጋ ላይ የጣሉ እኩይ ተግባራትን ሲያከናውን እንደነበር በዝርዝር አቅርበዋል፡፡
በአሁኑ ወቅትም የአሸባሪው ቡድኑ፣ መንግስት ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የወሰዳቸውን ተጨባጭ የሰላም አማራጭ ውሳኔዎችንና እርምጃዎች በመጣስ በአጎራባች የአማራና የአፋር ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ላይ ዳግም ወረራ መፈጸሙን ጠቁመው፤ መንግስት ተገዶ ወደ መከላከል እርምጃ እንደገባ ክቡር አምባሳደሩ አክለው ገልጸዋል፡፡
በፒተርማርዝበርግ ከተማና አካባቢው የሚገኝ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ በተለያዩ ጊዜያት ለቀረቡት አገራዊ ጥሪዎች ወቅታዊና ተጨባጭ ምላሾችን በመስጠት የሚታወቅ መሆኑን በማውሳት፣ እስከዛሬ ለተደረገው ተሳትፎ በሚሲዮኑ እና በራሳቸው ስም የላቀ ምስጋና ያቀረቡት አምባሳደሩ፤ በአሁኑ ወቅትም በአገራችን ላይ የተደቀነውን የህልውና አደጋ በተባባረ ክንድ ለመቀልበስ የሚደረገውን ተጋድሎ ማህበረሰቡ ህዝባዊ ደጀንነቱን ዳግም እንዲያረጋግጥ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በውይይቱ በርካታ የማህበረሰቡ አባላት የተሳተፉ ሲሆን፣ የቀረበውን ጥሪ ተከትሎ በሰጡት አስተያየት በአገራዊ ጉዳይ ላይ መቼም ቢሆን እንደማይደራደሩ በአጽንኦት ገልጸው፣ በአሁኑ ወቅትም በውስጥና በውጭ የቀናጀ የጠላት ሴራ በአገራችንና በህዝባችን ላይ የተጋረጠውን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ እየተደረገ ላለው ተጋድሎ የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
በውይይቱ ወቅትም ሚሲዮኑ ለዜጎች ልዩ ትኩረት በመስጠት መብቱና ክብሩን ለማስጠበቅ እየተደረጉ ያሉ ጥረቶች፣ ያጋጠሙ ችግሮችና የመፍትኤ አቅጣጫዎች፤ እንዲሁም የቆንስላና የኢሚግሬሽን አገልግሎቶችን ለዜጎች ተደራሽ ከማድረግ ጋር በተያያዘ ጠቃሚ ምክክር ተደርጓል፡፡
ሚሲዮኑ በሀገራዊ ወቅታዊ ሁኔታዎች ዙሪያ በደቡባ እና ደቡባዊ አፍሪካ ከሚገኙ ከፐብሊክና ዲጅታል ዲፐሎማሲ አደረጃጀቶች ጋር የሚያደርገው የተቀናጀ የዲጅታል ንቅናቄ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በአካል ወደ ማህበረሰባችን በመውረድ የጀመረውን የገጽ ለገጽ ምክክሮችን አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram