Sep 26, 2023
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከልዑካን ቡድናቸዉ ጋር በመሆን ደቡብ አፍሪካ የነባራቸዉን የስራ ጉብኝት አጠናቀዉ ወደ አገር ቤት ተመልሰዋል፣
በቆይታቸዉም ከደቡብ አፍሪካ የመከላከያ ሚንስቴር ሚንስትር Hon. Thandi Modise፣የመከላከያ ሰራዊት ዋና አዛዥ General Rudzani Maphwanya፣ከአየር ሃይል እና ልዩ ሃይል ዋና አዛዦች፣የጦር መሳሪያ እና ቴክኖሎጂ ላይ ከተሰማሩ ኩባንያዎች አመራሮች ጋር ተወያይተዋል።
 
የደቡብ አፍሪካ የመከላከያ ሰራዊት ዋና አዛዥል General Rudzani Maphwanya ለፊልድ ማርሻል ብርሃኑነ ጁላ ክብር የእራት ግብዥ ያደረጉ ሲሆን በዚህ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት ኢትዮጵያ የPan-Africanism ጀማሪ፣በቀኝ ግዛት ያልተገዛች ፣ ሌሎች አፍሪካዊያን ነጻ እንዲወጡ ፈር ቀዳጅ እና እገዛ ያደረገች መሆኗን ጠቅሰው በቀጣይ ወታደራዊ ትብብሮችን እና የልምድ ልውውጦችን በማጠናከር ትብብሩን የላቀ ደረጃ ለማድረስ ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።
 
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በበኩላቸው የሁለቱ አገራት ግንኙነት ረዥም ዘመናትን ያስቆጠረና ታሪካዊ መሆኑን ጠቅሰው ኢትዮጵያ በጸረ Apartheid ትግል ወቅት ለደቡብ አፍሪካ የነጻነት ታጋዮችና አመራሮች ስልጠናና ድጋፍ የሰጠች ሲሆን የሁለቱ አገራት ግንኙነት ዘማናትን ያስቆጠረ መሆኑን በማውሳት የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በብቃት በማስተናገድ ላደረገችው ትብብር ምስጋና አቅርበው በቀጣይም ወታደራዊ ትብብሮች እና የልምድ ልውውጦች በዚህ ጠንካራ መሰረት ላይ በመመስረት ከመቼውም ጊዜ በላይ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዎል።
 
የልዑካን ቡድኑ በቆይታዉ Mhakado Air Force Base እና Phalaborwa የልዩ ሃይል ማሰልጠኛ ማዕከል በመገኘት ዘመናዊ የአየር ሀይል አዉሮፕላኖችን እና የልዩ ሃይል አደረጃጀቶችንና ትጥቆችን ጎብቷል።በዚህ ወቅት የልዩ ሃይል እና የአየር ሃይል ትዕይንት የቀረበ ሲሆን በመቀጠልም የሉካን ቡድኑ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ከሚገኙ የጦር መሳሪያ እና ቴክኖሎጂ ምርት ላይ ከተሰማሩ ኩብንያዎች ጋር የወታደራዊ ቴክኖሎጂዎች ዙሪያ እና የመከላከያ የማድረግ አቅም በተመለከተ ተወያይተዋል።
 
በቆይታዉ የልዑካን ቡድኑ የአፓርታይድ ሙዚየም እና ኔልሰን ማንዴላ ከመታሰራሳቸው በፊት ይኖሩ የነበረበትን ታሪካዊ መኖርያ ቤት የጎበኙ ሲሆን አፓርታይድ ሙዚየም ውስጥ የሚገኘውን ኢትዮጵያ ለኔልሰን ማንዴላ ያስታጠቀችውን ሽጉጥና የሰጠችውን የኢትዮጵያ ፓስፓርት መመልከት ችለዋል።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram