(ሰኔ 27 ቀን 2014ዓ/ም አዲስ አበባ): የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክብር አምባሳደር ብርቱካን አያኖ በቦሌ አለምአቀፍ አዉሮፕላን ማረፊያ በመገኝት ለእንግዶች አቀባበል አድርገዋል ።
ክብርት ሚኒስትር ድኤታ አምባሳደር ብርቱካን እንግዶችን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ፣ዲያስፖራዎች ስለ አገራቸዉ የተሞላ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ለማስቻል ፣በልማት ፣ በኢንቨስትመንት በአገር ገፅታ ግንባታ ዘርፍ እንዲሳተፉ፥
እንዲሁም በአገራቸው ጉዳይ ቀጥተኛ ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማስቻል በዚህ ዓመት በርካታ ቁጥር ያላቸዉ ትዉልደ ኢትዮጵያዉያን ዲያስፖራዎች ወደ አገራቸዉ በመግባት ተሳትፎ ሲያደርጉ መቆየታቸዉን አስታዉሰዋል ።
የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክቡር ሙሃመድ እንድሪስ ( ዶ/ር ) በአቀባበሉ ላይ በመገኘት የሁለተኛው ዙር ከኢድ-እስከ- ኢድ አከባበር በይፍ ተጀምሯል እንግዶችም እየገቡ ነዉ ብለዋል ። መርሃ- ግብሩ በተለያዩ ስነ-ስርዓቶች በአዲስ አባባ አና በክልሎች እንደሚከበር ገልፀዎል።
የበደር ኢትዮጵያ አለምአቀፍ የሙስሊሞች ድርጅት ፕሬዝዳንት አቶ አህመድ ወርቁ የማህበሩ አባላት ጥሪዉን በመቀበል እና በቀጣይ ተሳትፎቸዉን ለማሳድ አዲስ አበባ መግባታቸዉን ተናግረዋል ።
በሰሜን አሜሪካ ነዋሪ በሆኑ ትዉልድ ኢትዮጵያዉያን የተመሰረተው በድር አለምአቀፍ የኢትዮጵያን ሙስሊሞች ድርጅት ከተመሰረተ ከ22 ዓመት በላይ አስቆጥሯል ።
በተመሳይ ከካናዳ እና በተለያዬ የዉጭ አገራት የሚገኙ የዲያስፖራ የአደረጃጀቶች ወደ አገራቸዉ ጥሪውን ተቀብዉ እየገቡ ይገኛሉ ።
ከተለያዩ ክፍለ አለማት የሚገኙ ኢትዮጵያ ከመጀመሪያው የኢድ በዓል አከባበር ጀምሮ ወደ አገራቸዉ በመግባት በተለያዬ መረሃ ግብሮች መሳተፋቸዉ ይታወሳል ።