16ኛው የሰንደቅ ዓለማችን ቀን “የሰንደቅ ዓለማችን ከፍታ ለህብረ-ብሔራዊ አንድነታችንና ሉአላዊነታችን ዋስትና ነው” በሚል መሪ ሀሳብ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ፣ በኢትዮጵያ ኤምባሲ አዘጋጅነት የዲያስፖራ ተወካዮች፣ በፕሪቶሪያ የዩንቨርስቲ የተማሪዎች ተወካዮች እና የኤምባሲው ሰራተኞች በተገኙበት ዛሬ ጥቅምት 5 ቀን 2016 ዓ/ም በድምቀት ተከብሯል፡፡
በበዓሉ ላይ መልዕክት ያስተላላፉት ክብርት ወ/ሮ ደሴ አለባቸው፣ ምክትል የሚሲዮኑ መሪ ባሰሙት ንግግር፡- አገራችን በዓለም አገራት ታሪክ ውስጥ ጥንታዊት በማንም ቅኝ ያልተገዛች ብቸኛዋ አፍሪካዊ አገር ናት ብለዋል፡፡ አያይዘውም፣ አገራችን ኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዜ የመጡ ጠላቶቿን አሳፍራ ከመመለሷም በላይ ለበርካታ አፍሪካዊያን የነጻነት ተምሳሌት ሆና ኖራለች፡፡ በመሆኑም የሰንደቅ ዓላማችን ቀለሞች ለብዙ አፍሪካዊያን ሰንደቅ ዓላማ መመስረት እንደ መነሻ ሆኖ እንዳገለገለ ገልጸዋል፡፡
የ16ኛው የሰንደቅ ዓላማ አከባባር ዋናው ዓላማም በሰንደቃችን ዙሪያ ህብረ- ብሔራዊ አንድነትን በማጠናከር ለኢትዮጵያ ሉአላዊነት ሀገራዊ ፍቅርና ክብር ለማሳየት ያለመ ነው፡፡ አገራችን ከ League of Nation እስከ United Nations ምስረታ የተሳተፈች የአፍሪካ አንድነት ድርጅት/ ህብረት መስራች ሆና በራሷ ሰንደቅ ዓላማ ሲትከበር የኖረች ናት፡፡ ስለሆነም ይህም ትውልት አንድነቷንና ክብሯን ጠብቆ ለቀጣዩ ትውልድ በክብርና በዝናዋ ልክ እንዲያስተላልፍ ይጠበቃል ብለዋል፡፡
ሰንደቅ ዓላማችን ከቃልና ከቀለም ባለፈ አንድ አድርጎን የያዙ መሠረታዊ የማንነቶቻቻን መገለጫ ፣ የአንድነታችን፣ ሉአላዊነታችን እና የክብራችን መገለጫ እምነት፣ ማህተብና ምልክት መሆኑ በዝግጅት ወቅት በሰፊው ተነስቷል፡፡ በመሆኑም ሁሉም ችግሮቻችን ከሰንደቅ ዓላማችን በታች በመሆናቸው በውይይትና መግባባት እየፈታን እንሄዳለን፡፡ በመሆኑም ለህብረ-ብሔራዊ አንድነት እና ለሉአላዊ ነችን የሰንደቅ ዓላማችን መንፈስ የማዕዘን ድንጋይ አድርገን እንደምንገነባው እና በየተሰማራንበት የስራ መስክ ሁሉ ድርሻችንን እንደምንወጣ መግባባት የተፈጠረበት የበዓል ዝግጅት ሆኖ ተካህዷል፡፡
ኢትዮጵያ ታፍራና ተከብራ እንዲትኖር ያደረጓት በደምና በአጥንታቸው መስዋትነት ለዚህ ትውልድ ያስተላለፏት ባለ ኩሩ ታሪክ ባለቤት የሆኑ ህዝቦች ያሏት ድንቅ አገር ናት፡፡ በመሆኑም ብሐራዊ አንድነታችንና ሉአላዊነታችን በሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ እየደመቀ እንዲሄድ እኛ ዜጎች ድርሻችንን እንወጣለን የሚሉ አስተያየቶች ከበዓሉ ተሳታፊዎች ተንጸባርቀዋል ፡፡
ጥቅምት 5 ቀን 2016 ዓ/ም
ፕሪቶሪያ የኤፊዲሪ ኤምባሲ