በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ በሚገኘው በ55ኛው Africa National Congress( ANC) ኮንፈረንስ ላይ የብልፅግና ፓርቲ ልኡካን ቡድን በመሳተፍ ላይ ነው።
ብልፅግና ፓርቲ እና የደቡብ አፍሪካው Africa National Congress ፓርቲ ዘላቂ የሆነ የሁለቱን ህዝቦች ትስስር ይበልጥ ሊያጠናክር የሚችል ግንኙነት በመመስረት ላይ ይገኛሉ።
ብልፅግና ፓርቲ ከፓርቲው የቀረበለትን ጥሪ በመቀበል ታሪካዊ የሆነውን ግንኙነት ለማጠናከር በ55ኛው የፓርቲው ኮንፍረንስ ላይ እንዲሳተፉ ተወካዮቹን ልኳል።
የፓርቲያችን ተወካዮችም የአጋርነት እና የአብሮ ሰራተኝነት መልእክታቸውን በኮንፍረንሱ ላይ አስተላልፈዋል።
ከፓርቲው ኮንፍረንስ ተሳታፊነት በተጨማሪ ከደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲርሊ ራማፎሳ ጋር ተገናኝተዋል።
ደቡብ አፍሪካ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ተፈጥሮ የነበረውን ችግር ለመፍታት ላበረከተችው አስተዋፆ ላቅ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።በፕሪቶሪያ የተፈረመውን ስምምነትም ለመፈፀም ብልፅግና ፓርቲ በከፍተኛ ቁርጠኝነት እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝም ገልፀዋል።