ክቡር አምባሳደር ዶ/ር ሙክታር ከድር ከቦትስዋና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር Bilateral Diplomacy Deputy Permanent Secretary ከሆኑት Ambassador Clifford Maribe እና የስራ ባልደረባቸው ጋር ስለሀገራችን ወቅታዊ ጉዳይ እና ቀጣይ በጋራ በሚከናወኑ ተግባራት ዙሪያ ተወያዩ።

 
ክቡር አምባሳደር ዶ/ር ሙክታር በዚህ ወቅት የሀገራችንን ወቅታዊ ሁኔታዎች እንዲሁም አህጉራዊ እና ዓለም ዓቀፋዊ ጉዳችን ከማብራራት ባሻገር በሀገራችንና በቦትስዋና መካከል መከናወን ባለባቸው ተግባራት ዙሪያ ገምቢ ውይይት አካሂደዋል።
 
ከግማሽ ምዕተ-ዓመት በላይ ባስቆጠረው የሁለቱ አገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የአገራት መሪዎች ይፋዊ ጉብኝት መከናወኑ ፣ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን መመስረቱ፣የተለያዩ ስምምነቶች መፈራረማቸው፣የአዲስ አበባ እና የጋቦሮኒ ከተሞች ጉድኝት ስምምነቶት ተጠቃሽ መሆናቸውን ክቡር አምባሳደር በዚህ ወቅት አብራርተዋል።
ይህንኑ የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከርም እ.ኤ.አ ከሜይ 29 ቀን 2018 ጀምሮ ክቡር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ፋንታን በቦትስዋና ኢትዮጵያ የክብር ቆንስል አድርጋ መሾሟን፤ በአሁኑ ወቅት በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ስለተደረገላቸው ድጋፍ በማመስገን፤በቦትስዋና የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ለአገሪቱ እያበረከቱ ያለውን አስተዋጽኦ በተመለከተም አስረድተዋል።
 
ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይን አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የተከሰተውን ጦርነት በሠላም ለመቋጨት በአፍሪካ ኅብረት መሪነት ከሥምምነት ላይ ተደርሶ ወደ አፈጻጸም መሸጋገሩን፣ ስለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ፣ስለኢትዮ-ሱዳን ድንበር ጉዳይ የኢትዮጵያን መንግስት አቋም የተመለከተ ማብራሪያ በመስጠት በቀጣይ በጋራ ሊከናወኑ የሚገቡ ተግባራትንም አመላክተዋል።
ክቡር አምባሳደር ኢትዮጵያ በፈታኝ ሁኔታ ውስጥ በቆየችባቸው ጊዜያት ወንድምና እህት የአፍሪካ ህዝቦችና መንግስታት ላሳዩት ድጋፍ በኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ስም ምስጋና አቅርበዋል።
የቦትስዋና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር Bilateral Diplomacy Deputy Permanent Secretary የሆኑት Ambassador Clifford Maribe በበኩላቸው ለማብራሪያው ምስጋናቸውን በማቅረብ በወቅታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታ ላይ የተሰጠው ገለጻ ግልጽነት እንደፈጠረላቸው እንዲሁም በታላቁ የህዳሴ ግድብ እና በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ጉዳይ ላይ ኢትዮጵያ የያዘችው አቋም ትክክለኛ መሆኑን በመጠቆም የተሰጣቸውን መረጃ ለበላይ አካላት እንደሚያስተላልፉ አስታውቀዋል።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram