በኢፌዴሪ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ክቡር ዶክተር ሙክታር ከድር በደቡብ አፍሪካ የሱዳን ሪፓብሊክ አምባሳደር ከሆኑት H.E. Osama Mahjoub Hassan Dirar ጋር በሁለትዮሽ፣ አህጉራዊና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ጠቃሚ ውይይት አካሂደዋል፡፡
 
ክቡር አምባሳደር ዶክተር ሙክታር ከድር በዚሁ ወቅት ታሪካዊ የሆነውና ረዥም ዕድሜን ያሰቆጠረው የኢትዮጵያና የሱዳን የወዳጅነት ግንኙነት በጠንካራ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት መሰረት ላይ የተገነባ፣ በባህል ትስስር የተጋመደ፣ በመልካም ጉርብትናና እህትማማችነት ተምሳሌት የሆኑ ህዝቦች የሚገኙባቸው አገራት መሆናቸውን ገልጸዋል። የሁለቱን አገሮች የኢኮኖሚ ትብብር ለማጎልበት በመሰረተ ልማት ዝርጋታ፣ በመንገድ ልማትና በኤሌክትሪክ አቅርቦት ትስስራቸውን ለማጠናከር እየተሰራ ያለው ስራ በተምሳሌትነቱ የሚጠቀስ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡
 
H.E. Osama Mahjoub Hassan Dirar Ambassador of the Republic of Sudan to the Republic of South Africa በበኩላቸው ክቡር አምባሳደር ዶክተር ሙክታር ከድር ስለ ሁለቱ እህትማማች አገሮች የሰጡት አስተያየት ትክክለኛና እርሳቸውም የሚቀበሉት መሆኑን በመግለጽ ጀምረው፣ ኢትዮጵያና ሱዳን የጥንት ስልጣኔ ባለቤቶች መሆናቸውን፣ረዥም ድንበር የሚጋሩ ህዝቦች መሆናቸውን፣ የህዝብ ለህዝብ ግንኙታችን ሁሌም ቢሆን መልካም ሆኖ ለሽህ ዓመታት የዘለቀ፣ የኢትዮጵያን ባህል እንደሚያውቁና እንደሚወዱ፣ ሱዳናውያን የኢትዮጵያን ልብስ እየለበሱ የኢትዮጵያን ምግቦች እያጣጣሙ የኖሩ ህብረታቸው የጎላ ህዝቦች ግንኙነት በዚሁ መልኩ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ፣ ፈተናዎች ቢያጋጥሙንም ወደ ግጭት የሚወሰደን ጉዳይ እንደሌለ፣ ሁለቱ የአፍሪካ ቀንድ ትልልቅ አገሮች በቀጠናው በጎ ሚና ሊጫወቱ ይገባል ብለው በጽኑ እንደሚያምኑ፣ የኢትዮጵያ ሰላም የሱዳን ሰላም ነው በሚል ዕምነት ሱዳን የፕሪቶሪያውን ስምምነት እንደምትደግፍ፣ የሁለቱ ኤምባሲዎች ቅንጅት እንዲጠናከር እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram