ክቡር አምባሳደር ዶ/ር ሙክታር ከድር በ East London International Convention Center እ.አ.አ. ሴፕቴምበር 14-15 ቀን 2022 International Trade- A leveler to Economic Recovery በሚል መሪ-ቃል ለአራተኛ ጊዜ በተካሄደው የEastern cape Export Symposium ላይ የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት ዕድሎችና ማበረታቻዎችን አስተዋወቁ። ክቡር አምባሳደር 35 ደቂቃ የፈጀ የተደራጀ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን በዚሁ መድረክ ላይ DID YOU KNOW ETHIOPIA? የሚል የኢትዮጵያን መልካም ገጽታ የሚገነባና ተመራጭነቷን የሚያሳይ አጭር ቪዲዮ በተሳታፊዎች እንዲታይ ተደርጓል ።
 
ክቡር አምባሳደር ዶ/ር ሙክታር ከድር በሲምፖዚየሙ ላይ ባደረጉት ንግግር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኢትዮጵያ እያካሄደች ባለችው ሁለንተናዊ የኦኮኖሚ ሪፎርም ከመቼውም ጊዜ በላይ ለውጭ ለባለሃብቶች ምቹ የኢንቨስትመንት መዳረሻ እንደሆነች ያስረዱ ሲሆን በተለይም መንግስት ትኩረት በሰጣቸው የኢነርጂ ፣ማዕድን፣ አግሮ ፕሮሰሲንግ፣ ጨርቃ ጨርቅ እና ጋርመንት፣ ቱሪዝም፣ ቆዳ እና የቆዳ ውጤቶች እንዲሁም ፋርማሲውቲካል የኢንቨስትመንት መስኮች የተሻሻሉ የኢንቨስትመንት ህጎች እና አመቺ መሰረተ-ልማት ዝርጋታዎችና ማበረታቻዎች በሰፊው በማብራራት በEastern cape የሚገኙ ኩባንያዎች ዕድሉን በመጠቀም ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጋብዘዋል። በወቅቱም ኢትዮጵያን በተመለከተ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች ተገቢ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ሲምፖዚየሙ ወደፊት በዓለማቀፍ ደረጃ ለሚካሄዱ ተመሳሳይ መድረኮች ትምህርት የተገኘበትና የተሳካ ነው፡፡
 
ሲምፖዚየሙ ዓለም -አቀፉ ንግድ ላይ እየታዩ ያሉትን ተግዳሮቶች ለመመከት እንዲቻል አዳዲስ ስትራቴጂዎችን ለመቀየስ ያለመ ሲሆን በዚህም በEastern Cape ያሉ ኩባኒያዎች ነባርና አዳዲስ ገበያዎች ጋር ያላቸውን ትስስር በማጠናከር የገበያ ዕድሎችን እንዲጠቀሙ የሚያበረታታ ሲሆን በርከት ያሉ ታዋቂ ግለሰቦችና ተቋማት በአካልም ኦንላይንም የተሳተፉበት ነው፡፡

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram