አዲስ አበባ ሚያዝያ 15/2015 (ኢዜአ)፦ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከደቡብ አፍሪካ የዓለም አቀፍ ግንኙነት እና ትብብር ሚኒስትር ናሌዲ ፓንዶር ጋር በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት አተገባበር ዙሪያ መወያየታቸው ተገለፀ።
 
የሰላም ስምምነቱ በተገቢው መንገድ እንዲሄድ የደቡብ አፍሪካ መንግስት ላደረገው ድጋፍ ያመሰገኑት አቶ ደመቀ፤ የኢትዮጵያ መንግስት ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ በጦርነት ጉዳት የደረሰባቸው አካባቢዎችን መልሶ ለማልማት እና ነዋሪዎችን ለማቋቋም የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።
 
ሚኒስትር ናሌዲ ፓንዶር በበኩላቸው ደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ የሰላም ሂደት አካል በመሆኗ ኩራት እንደሚሰማቸው ገልፀዋል።
 
ለአፍሪካ ችግሮች የአፍሪካ መፍትሄዎች በመስጠት ግጭቶችን ከመፍታት ባለፈ በመልሶ ግንባታ እና በመልሶ ማቋቋም ስራዎች ላይ ትከረት መሰጠት እንደሚያስፈለግ ጠቅሰዋል።
 
ደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ የመልሶ ማቋቋም ስራዎችን በተለይም በትምህርት ዘርፍ ላይ ለማገዝ ፍላጎት እንዳላት መግለፃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram